Loading...

ፖርቹጋል በአውሎ ንፋስ ምክንያት ከ200 በላይ በረራዎችን ሰረዘች፤ ትምህርት ቤቶችን ዘጋች

Portugal cancels 200-plus flights, shuts schools as Storm Charles hits

ከባድ ዝናብና ኃይለኛ ንፋስ በቀላቀለ አውሎ ንፋስ የተመታችው ፖርቹጋል ከ200 በላይ በረራዎቸን ለመሰረዝ፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ሱፐርማርኬቶችንና የንግድ ተቋማትንም ለመዝጋት መገደዷን ሮይተርስ ዘግቧል።

አውሎ ነፋሱ በደቡባዊው የአልጋርቭ ክልል ከመድረሱ በፊት ኃይሉ ቢቀንስም፣ ባለሥልጣናት ድንገተኛ ጎርፍ፣ ኃይለኛ ንፋስና የባሕር ሞገድ አደጋዎች ሊከሰቱ ይችላሉ በሚል ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ ናቸው።

የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ቡድኖች 538 ክስተቶችን መመዝገባቸውና በማዴይራ ደሴት የነፍስ አድን ስራ ማከናወናቸው ተገልጿል።

አዲሱ አውሎ ነፋሱ በፖርቱጋልና ጎረቤቷ ስፔን ላይ ላለፉት ቀናት ከባድ ዝናብ ካስከተለው ብሩና ከተባለው አውሎ ንፋስ በኋላ የመጣ ነው። ባለስልጣናት ከባድ ዝናብ እንደሚቀጥል ሲያስጠነቅቁ፣ ግድብ ይሞላል ብለው የሰጉ ከ3000 በላይ ከአካባቢው ወጥተዋል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

More News

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው