Loading...

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን ዘላቂነትና አስተማማኝነት የሚያረጋግጠው የቻይናና ኢትዮጵያ ስምምነት

China signs agreement with Ethiopia to ensure sustainability and reliability of Ethio-Djibouti railway

ቻይና በግንባታው ሂደት ቀዳሚ አስተዋጸኦ ላደረገችው የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመሮ የሚውል የ15 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት በመፈራረም፣ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ድጋፍ ከአንድ ጊዜ የመሰረተ ልማት ግንባታ የተሻገረ እንደሆነ አሳይታለች።

ይህ የባቡር መስመር ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አመት ቢያስቆጥርም፣ ቻይና ለዘላቂነቱና አስተማማኝነቱ ትኩረት በመስጠት ነው ድጋፉን ያደረገችው።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ትዕግስት ፍስሃ እና በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሊዩ ዚያኦጓንግ መፈረማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ድጋፉ የባቡር መስመሩን ዘላቂነት፣ አስተማማኝነትና የሥራ ቅልጥፍና ለማሳደግ እንደሚውል የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር አስታውቋል።

የገንዘብ ድጋፉ የኤሌክትሪክ ባቡሮችን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎችን፣ የዋናውን የባቡር መስመር ደህንነት ለማሻሻል የሚያገለግሉ የሐዲድና የጣቢያ መሣሪያዎችን ያካትታል።በተጨማሪም ለመደበኛ የሐዲድ ቁጥጥርና ጥገና የሚያገለግሉ አነስተኛ ማሽነሪዎች ለማቅረብ እንደሚውል ተገልጿል።

ሚኒስቴረ አክሎም ስምምነቱ በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን ጠንካራ የኢኮኖሚና የልማት ትብብር የሚያጠናክር ነው ብሏል።

4 ቢሊዮን ዶላር የወጣበት ኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር

ቻይና በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት ግንባታ ጉልህ ተሳትፎ እያካሄዱ ካሉ ሀገራት በቀዳሚነት የምትጠቀስ ሀገር ነች። ቻይና ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ጋር የሚጣመው አህጉራዊ ትስስር ለመፍጠር የሚያሰችል የቤልት ኤንድ ሮድ አ(BRI) ይፋ አድርጋች። የባቡር መስመር ዝርጋት የዚህ ኢኒሼቲቭ አንዱ አካል ነው።

እአአ ከ2000 እስከ 2023 ድረስ ባቡበርን ጨምሮ በአፍሪካ ለሚደረጉ የመሰረተልማት ዝርጋታዎች የ182.28 ቢሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ ማድረጓን መረጃወች ያለመለክታሉ።በዚህ ጊዜ ውስጥ ከተሰሩት ቀልፍ የአፍሪካ የባቡር መሰረተልማት ውስጥ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን አንዱ ነው።

ወደብ አልባዋን ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ወደቦች የሚያገናኘውንና 756 ኪሎሜትር የሚረዝመው ይህ የባቡር መስመር፣ ከፍተኛ ኤኮኖሚ ፋይዳ ያለው ነው። የኢትዮጵያ የባህርና ሎጂስቲክ ሚኒስትር መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በ2025/2026 የበጀት አመት የኢትዮጵያ 96.7 በመቶ የሚሆነው የወጭና የገቢ ንግድ የሚመላለሰው በጅቡቲ ወደብ ነው። ስለሆነውም ይህ የባቡር መስመር፣ ለኢትዮጵያ የወጭና የገቢ ንግድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ያመላክታል።

ፕሮጀክቱ በ4 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ወጭ የሸፈነ ሲሆን የቻይና ኢምርት ኤክስፖርት (ኤግዚም)ባንክ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነውን በብድር መልክ ድጋፍ አድርጓል። ግዙፍ የሆኑ የቻይና ተቋራጮች ደግሞ በግንባታ ስራ ተሳትፎ አድርጠዋል።

በመሰረተልማት ዝርጋታና በንግድ ያልታጠረው የቻይናና የኢትዮጵያ ትብብር በአሁኑ ወቅት ወደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስና (ኤአይ) በድጅታል ቴክኖሎጂ ዘርፎች ተሸጋግሯል። በኤአይ ዘርፍ የላቀ እውቀትና በርካታ ኩባንያዎች ከሏት ቻይና ጋር መተባበር ለኢትዮጵያ የዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ጉልህ አስዋጽኦ ይኖረዋል።ሁለቱ ሀገራት ከኤይ ልማት በተጨማሪ ቴክኖሎጂው ለታለመለት እንዲለው በማድረግና በማስተዳደር ለመተባበር መስማማታቸው ይታወሳል።

የዜሮ ታሪፍ ፖሊሲ

ቻይና ባለፈው ሚያዝያ ወር መጨረሻ ይፋ ያደረገችው 53 ሀገራትን ተጠቀሚ የሚያደርገው፣ የዜሮ ታሪፍ ፖሊሲ፣ የቻይናና ኢትዮጵያ ትብብርን የበለጠ የሚያጠናክር ነው። ፖሊሲው ኢትዮጵያ የቡና፣ የአበባና ፍራፍሬ አምራቾች ወደ ሰፊው የቻይና ገበያ እንዲደርሱ የሚያደርግ ነው። አሜሪካ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የቀረጥ ነጻ እድሎ እየሰረች ባለችበት ወቀት ተግባራዊ የተደረገው የቻይና ዜሮ ታሪፍ ፖሊሲ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ወሳኝ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

More News

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው