ከጊዛ ወደ ፋዩም ይጓዝ የነበረ ባቡር ከካይሮ ወደ አስዋን በሚጓዝ ሌላ ባቡር የኋላ ክፍል ላይ በመጋጨቱ አንዳንድ የባቡሩ ክፍሎች ከሐዲዱ ወጥተዋል።
የግብፅ ጤና ሚኒስቴር 72 አምቡላንሶች ወደ አደጋው ቦታ በመላክ ተጎጂዎችን ወደ አቅራቢያ ሆስፒታሎች ማጓጓዛቸውን ገልጿል።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ የአደጋው መንስኤ እንዲጣራና ተጠያቂዎች በህግ እንዲጠየቁ አስቸኳይ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዋል።
የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ቡድኖች የተጎዱትን የባቡር ክፍሎች ለማንሳትና የባቡር መስመሩን አገልግሎት ለማስቀጠል እየሰሩ ነው። የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ ግን እስካሁን አልተለየም።
የዜናው ምንጮች
ሮይተርስ: ኤፒ እና የግብፅ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት











