Loading...

የቻይና እና አፍሪካ ትብብር ከ 5 አመት በኋላ ሲገመገም

Five Years On: Assessing the Promise of China–Africa Cooperation

ስምንተኛው የቻይና እና አፍሪካ ትብብር ፎረም(FOCAC) የሚኒስትሮች ስብሰባ በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር ከተካሄደ አምስት አመት ሆኖታል። ከአምስት አመት በኋላ ቻይና እና አፍሪካ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በጋራ የልማት ትልሞች ላይ የተመሰረተውን አጋርነታቸውን ይበልጥ እያጠናከሩ ይገኛሉ።

ኅዳር 29 ቀን 2021 (እ.ኤ.አ.) በተካሄደው ጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የግኙነቱን ታሪካዊ መሰረት ሲያወሱ፣ ቻይና እና አፍሪካ “ኢምፔሪያሊዝምን እና ቅኝ አገዛዝን በመታገል የማይበጠስ ወንድማማችነትን መስርተዋል፤ ወደ ልማትና ዳግም መነቃቃት በምናደርገው ጉዞም ልዩ የትብብር መንገድ ጀምረዋል” ሲሉ ነበር የተናገሩት።

ፕሬዝዳንት ዢ አክለውም “ቅን ወዳጅነትና እኩልነት፣ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር፣ ፍትሃዊነትና ርትዕ፣ እንዲሁም ከጊዜው ጋር መሻሻልና ግልጽነትና አካታችነት” በቻይና እና አፍሪካ መካከል ጠንካራ የግንኙት እንዲኖር ያስቻሉ ቁልፍ መርሆዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዳካር ጉባኤ ላይ ፕሬዝደንት ዢ ጤናን፣ ግብርናን፣ ንግድን፣ ኢንቨስትመንትን፣ ዲጂታል ፈጠራን፣ አረንጓዴ ልማትን፣ የአቅም ግንባታን፣ የባህል ልውውጦችን እንዲሁም ሰላምና ደህንነትን የሚያካትቱ ዘጠኝ መርሃ ግብሮችን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ከአምስት ዓመታት በኋላ የታዩት በርካታ ተጨባጭ ክንውኖች እነዚህ ቃል ኪዳኖች ወደ ተግባራዊ ትብብር መሸጋገራቸውን ያሳያሉ። ለዚህም ጉልህ ምዕራፍ የሚሆነው ቻይና ከግንቦት 1 ቀን 2026(እ.ኤ.አ) ጀምሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላላት ለሁሉም 53 የአፍሪካ ሀገራት ከቀረጥ ነጻ የንግድ እድልን ማስፋፋቷ ነው። ይህ እርምጃ ቀደም ሲል በዝቅተኛ የእድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ተዘርግቶ በነበረው አሰራር ላይ የተገነባ ሲሆን፣ የአፍሪካ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ወደ ሰፊው ቻይና ገበያ እንዲገቡ ሰፊ ዕድል ከፍቷል።

የመሰረተ ልማት ትስስርም የአጋርነቱ ዋነኛ ምሰሶ ሆኖ ቀጥሏል። ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነው በኅዳር 2025 (እ.ኤ.አ.) በቻይና የተጀመረው እና 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተደረገበት የ1,860 ኪሎ ሜትር የታንዛኒያ-ዛምቢያ የባቡር መስመር (TAZARA) ማሻሻያ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ ዳሬሰላምን ከዛምቢያ የመዳብ ቀበቶ (Copperbelt) ጋር የሚያገናኘውን ታሪካዊ የባቡር መስመር በማዘመን፣ ቀጠናዊ ንግድንና የትራንስፖርት ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ይህ ትብብር ከተለመዱት ዘርፎች ባለፈ ወደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ልማት እና ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዳደር ዘርፎች ተሸጋግሯል።

እነዚህ ክንውኖችና ሌሎች በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት በቻይና መንግስት የተሰሩት ፕሮጀክቶች፣ ዢ በዳካር ያስቀመጡትን አቅጣጫ ማለትም የገበያ ተደራሽነትን ማስፋትን፣ ትስስርን ማሻሻልን፣ የቴክኖሎጂ ትብብርን ማሳደግን እና የአፍሪካን የልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መደገፍን በግልጽ የሚያንጸባርቁ ናቸው።

ይሁን እንጂ የትብብሩ የመጨረሻ ስኬት የሚለካው ለአፍሪካ ኢንዱስትሪያላይዜሽን፣ ለአካባቢው የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለኢኮኖሚ ብዝሃነት በሚያበረክተው ተጨባጭ አስተዋጽኦ ይሆናል።

ከዳካር ጉባኤ በኋላ፣ የቻይና-አፍሪካ ትብብር ከቃል ኪዳንና መግለጫዎች ባለፈ እያደገ ወደመጣ የንግድ፣ የዲጂታል እና የመሰረተ ልማት ተነሳሽነቶች ተሸጋግሯል። ቀጣዩ ፈተና እነዚህን ስኬቶች ለአፍሪካ ሀገራትና ህዝቦቿ ዘላቂ ብልጽግናን እንዲያመጡ ማረጋገጥ ይሆናል።

የቻይና እና አፍሪካ ትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ስብሰባዎች ቀደም ሲል የተገቡ ቃልኪዳኖች መፈጸማቸውን ለመገምገም፣ ቃልኪዳኖችን ለማደስ፣ የትብብር ዘርፎችን ለማስፋፋት፣ እየመጡ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታትና አፈጻጸምን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ከዳካሩ ስብሰባ ከሶስት አመት በ2024 (እ.ኤ.አ) በቻይና ቤጂንግ የተካሄደው ዘጠነኛው የ FOCAC የሚኒስትሮች ስብሰባ፣ የቻይና እና የአፍሪካ መሪዎች ለተፈናዎች የማይገበር ትብብር ለመገንባት ቁርጠኝነታቸውን የገለጹበት፣ ቅድማያ የሚሰጣቸውንና ስትራቴጂካዊና አዳዲስ የትብብር ዘርፎችን የለዩበት ነበር።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው