Loading...

የኢትዮጵያ መንግስት የናፍጣ ስርጭት መጠንን ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት መለሰ

መንግስት እለታዊ የናፍጣ አገልግሎት መጠንን ከዛሬ ጀምሮ ከኢራን ጦርነት በፊት ወደነበረበት መመለሱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት የሀገሪቱን እለታዊ የናፍጣ ስርጭት መጠን ኢራንን፣ አሜሪካንንና እስራኤልን ያሳተፈው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት ወደነበረበት መመለሱን ኢቢሲ የፋይናንስ ሚኒስትሩን አቶ አህመድ ሺዴን ጠቅሶ ዘግቧል።

ጦርነቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የነዳጅ አቅርቦት ላይ መስተጓጐልንና የዋጋ ጭማሪ ቀውስን አስከትሏል። በእጥረቱ ምክንያት ወደ 4.5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ብሎ የነበረው እለታዊ የአቅርቦት መጠን ወደ 9 ሚሊዮን ሊትር ከፍ እንዲል ተወስኗል

ሚኒስትሩ እንደገለጹት መጠኑን ለማስተካከል ከዛሬ ጀምሮ ከጅቡቲ ከፍተኛ መጠን ያለው ናፍጣ ወደ መሀል ሀገር እየጓጓዘ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የአውሮፕላን ነዳጅ አቅርቦት መጠን በጦርነቱ ምክንያት አልተስተጓጎለም ያሉት ሚኒስትሩ መንግስት በአሁኑ ወቅት ለነዳጅ ቀድሞ ከነበረው በተጨማሪ በየወሩ 20 ቢሊዮን ብር እየደጎመ እንደሚገኝ ገልጸዋል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው