የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በነገው እለት ጥር 13፣ 2818 ዓ.ም. በሚያካሂደው 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ኢትዮጵያ ከቻይና፣ ከብራዚልና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ወንጀለኞች አሳልፎ ለመስጠት የገባቻቸውን ስምምነቶች ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክርቤቱ ጉባኤውን አስመልክቶ ባወጣው አጭር መግለጫ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ከመረመረ በኋላ ረቂቅ አዋጆቹን እንደሚያጸድቁ ይጠበቃል ብሏል።
ረቂቅ አዋጆቹ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የገባችውን የወንጀል ጉዳዮች የጋራ ትብብርንና ፍርደኞችን የማስተላለፍ ስምምነቶች የሚያጸኑ ሲሆን፣ ከብራዚል ጋር ፍርደኞችን ከደቡብ አፍሪካ ጋር ደግሞ በወንጀል የሚፈለጉ ስዎችን አሳልፎ ለመስጠት ያስችላሉ።
ስምምነቶቹ መቼ ተፈረሙ?
ኢትዮጵያና ቻይና አንዳቸው ለሌላኛቸው ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት እንዲሁም በወንጀል ጉዳዮች ለመተባበር የተፈራረሙት ሚያዝያ 2018 ነበር። ስምምነቱ የተፈረመው አዲስ አበባ ነው።
የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስትርና የደቡብ አፍሪካ አለምአቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር በካሄዱት የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ወቅት ተፈላጊዎችን አሳልፎ ለመስጠት ሰኔ 2017 ተፈራርመዋል።
ባለፈው ታህሳስ ወር ኢትዮጵያ ፍርደኞችን አሳልፎ ለመስጠት ከብራዚል ጋር ይፋዊ ስምምነት አድርጋለች።











