Loading...

በኢትዮጵያ ወርቅን ጨምሮ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ተመርቆ ስራ ጀመረ

Ethiopia inaugurates Gold refinery industry at Bole Lemi - Opened by Prime Minister Abiy Ahmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት  በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባውን ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መርቀው ስራ ማስጀመራቸውን ፋና ዘግቧል።

በምረቃው ስነስርዓቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋብሪካው መገንባት ኢትዮጵያ ጥሬ እቃ ልካ በምትኩ የተሰሩ ምርቶችን በውድ የምታስገባበትን አካሄድ ለማስቀረት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ጥሬ ቡና ወደ ውጭ ተልኮ ታሽጎና ተቆልቶ በብዙ እጥፍ ተመልሶ የሚገዛበትን ውድ ዋጋ በአብነት አንስተዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስራዎች በታቀደላቸው ጊዜ ተጠናቀው ለህዝብ ይፋ እንደሚሆኑ ይህን ፋብሪካ በምሳሌነት አንስተዋል።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ወርቅ ስትልክ ያለማጣሪያ በመሆኑ 30 በመቶ የሚሆነው እንደ ቆሻሻ ተቆጥሮ ይቀነስ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ማጣሪያ ይህንን ችግር እንደሚቀርፍ ገልጸዋል።

ፋብሪካውም በዓመት እስከ 80 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ኤክስፖርት ማከናወን የሚያስችል ትልቅ አቅም ያለውና ከአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት አንዱ ነው ተብሏል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው