የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ የሚገኘውን ግብጻዊ ዲፕሎማት አህመድ ሞሃራም አህመድ ሶሊማንን በኢትዮጵያ “ተቀባይነት የሌላቸው” (Persona Non Grata) ሲል ማወጁንና በ48 ሰዓታት ውስጥ ሀገር ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን ዛሬ ምሽት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግብጻዊው ዲፕሎማት ከአገሪቱ እንዲወጡ የተወሰነበትን ዝርዝር ምክንያት በመግለጫው ላይ ባይጠቅስም፣ ውሳኔው የመጣው በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ባነሰረበት እና በቀንድ አፍሪካ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ውጥረት በነገሠበት አጣዳፊ ወቅት ነው።
ይህ እርምጃ ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት መወሰኗንና በአዲስ አበባ የሚገኙ 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች “ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፋቸው” በ48 ሰዓታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ካዘዘች ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የተከተለ ነው።
ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን መዝጋቷንና የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ማባረሯን ተከትሎ፣ የኤርትራ መንግሥት በምላሹ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉንም የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ ማቋረጧን ማስታወቋ ይታወሳል። የግብጽ መንግሥት የዲፕሎማቷን መባረር በተመለከተ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።












