Loading...

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ መንግስት ጋር 1.616 ቢሊዮን ዶላር የጤና ዘርፍ የእርዳታ ትብብር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች።

በስምምነቱ መሰረት አሜሪካ በሚቀጥሉት አምስት አመታት የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ለመደገፍ እስከ 1.016 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዲሁም በአፈጻጸም ላይ ተመስርቶ 150 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የምታደርግ ሲሆን ገንዘቡ በቀጥታ ከመንግስት ወደ መንግስት የሚተላለፍ ይሆናል።

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ለፕሮግራሙ ትግበራ እና ዘላቂነት ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት እስከ 450 ሚሊዮን ዶላር መድቧል።

የአምስት ዓመቱ የድጋፍ ስምምነት በኢትዮጵያ የበሽታ መከላከልን፣ የጤና ስርዓትቱ የመቋቋም አቅም እና የመንግስት ጤና ስርዓቶችን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ኢትዮጵያ የምታገኘው ለጤናው ዘርፍ የሚውል ድጋፍ ቀደም ሲል አሜሪካ ለኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ናይጄሪያ ካቀረበቻቸው ድጋፎችን ተከትሎ የተፈጸመ ነው። በቅድሚያ ስምምነት የፈጸመችው ኬንያ ስትሆን አሜሪካ 1.6 ቢሊዮን ዶላር ያህል ለመስጠት ስትስማማ ኬንያ ወደ 850 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለመመደብ ቃል ገብታለች።

ሩዋንዳ 228 ሚሊዮን ዶላር የአሜሪካን ድጋፍ ያገኘች ሲሆን የሩዋንዳ መንግስት በተመሳሳይ ተጨማሪ 70 ሚሊዮን ዶላር መድቧል።

አሜሪካ ለናይጄሪያ ያቀረችው 2.1 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሲሆን የናይጄሪያ መንግስት በበኩሉ ዘርፉ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መድቧል።

እነዚህ ስምምነቶች፣ ከኢትዮጵያ ጋር እንደተፈረመው ስምምነት ሁሉ፥ የትራምፕ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አሜሪካ መተግበር የጀመረችውን አዲስ ስትራቴጂ የሚያንጸባርቁ ናቸው። ይህም እንደ በፊቱ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አማካኝነት ሳይሆን ድጋፉ በቀጥታ ከመንግስት ወደ መንግስት የሚተላለፍ ይሆናል፥ እንዲሁም የአገራቱ አፈጻጸማመቸውን እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ነው።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው