Loading...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ክልል የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን አስታወቀ

Ethiopian Airlines Suspends Flights to Tigray Region amid Heightened Tensions

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል ባለው “ወቅታዊ ሁኔታ” ምክንያት ወደ መቐለ፣ አክሱም እና ሽሬ አውሮፕላን ማረፊያዎች የሚደረጉ በረራዎችን ማገዱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አየር መንገዱ የበረራ አገልግሎቱን ለማቋረጥ ያስገደዱትን ምክንያቶች በግልጽ ባይጠቅስም፣ እገዳው የተጣለው በፌዴራል መንግሥት እና በትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ህወሓት) መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ወቅት ነው። ቀደም ባሉት ጊዜያት የበረራ መቋረጥ የውጥረት መባባስ ምልክት ነበር።

ይህ ውሳኔ ሀገሪቱ ወደ ሌላ አጥፊ ግጭት ልትገባ ትችላለች የሚል የፍርሃት ስሜትም ፈጥሯል። ህወሓት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በይፋ ውድቅ ማድረጉንና በፌዴራል መንግሥት የሚደገፈውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር “የትግራይን ሕዝብ አልጠቀመም” በማለት ማገዱ ይታወሳል።

የፌዴራል መንግሥት እና ህወሓት ስምምነቱን በመጣስ እና የተደረሱትን ውሳኔዎች ወደ መሬት ለማውረድ “እግራቸውን በመጎተት” እርስ በርሳቸው ሲወነጃጀሉ ቆይተዋል። የፌዴራል መንግሥት ህወሓትን የኤርትራን መንግሥት ጨምሮ “ከኢትዮጵያ ጸረ-ኃይሎች ጋር ያብራል” በማለት መክሰሱም ይታወሳል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው