Loading...

ኢትዮጵያዊቷ ፎትዬን የባርሴሎና ማራቶንን በማሸነፍ በታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን ሰአት አስመዘገበች

ኢትዮጵያዊቷ የረጅም ርቀት ራጭ ፎትዬን ተስፋይ በመጀመሪያዋ የማራቶን ውድድር የባርሴሎናን ማራቶን 2:10:53 ሰአት በማሸነፍ  በታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን ሰአት ማስመዝገብ መቻሏ ተዘግቧል።

ሮይተርስ እንደዘገበው ፎትዮን ወድድሩን ያሸነፈችው ኬንያዊቷን አትሌት ጀፕኮሰጊ ኪፒሊሞን በመቅደም ነው። ሌላኛዋ የውድድሩ ተሳታፊ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘይነባ ይመር ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

ፎትዬን ከወድድሩ በኋላ “ዛሬ ልዩ ቀን ነው። የጠበቅሁት አልነበረም፤ ነገር ግን ጥሩ ነው”  ብላ መናገሯን ዘገባው ጠቅሷል።

“አላማዬ የአለም ሪከርድን መስበር ነበር፤ ነገርግን ከፍተኛ ነፋስ ነበር። በውድድሩ የመጨረሻ ዙር መፍጠን አልቻልኩም ነበር። ዛሬ አልተሳካልኝም፤ ወደፊት በሚኖሩ ውድድሮች ግን የአለም ክብረወሰንን ለመስበር እሞክራለሁ”።

ኬንያዊቷ አትሌት የጸረ-አበረታች ህጎችን በመጣሷ ምክንያት ለሶስት አመት እንዳትወዳደር እግድ ተጥሎባት ነበር። ኡጋንዳዊው አትሌት አቤል ቸላንጋት የወንዶችን ውድድር በ1ኛነት አጠናቋል

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው