Loading...

ኢራን በባህሬን የእስራኤል ኢምባሲ ላይ ጥቃት ፈጸመች

ኢራን ሌሊቱን በባህሬን የእስራኤል ኢምባሲና በንግድ ህንጻዎች ላይ ጥቃት ማድረሷ ተገለጸ።

እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ እየፈጸሙት ያለው የአየር ጥቃትና ኢራን የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ባሉባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ እያደረሰችው ያለው የበቀል እርምጃ ቀጠናውን ትርምስ ውስጥ ከቶታል።

በርካታ የባህረሰላጤው ሀገራት፣ የአረብ ሀገራት፣ ቱርክና አዘርባጃን ለቀጣናው ቀውስ ተጋላጭ ሆነዋል።

ኢራን በተለይ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ባለባቸው በባህሬን፣ በሳኡዲ አረቢያ፣ በአረብ ኢምሬትስና በኳታር እያደረገች ያለችው የሚሳይልና የድሮን ጥቃት አሁንም እንደቀጠለ ነው።
የሳኡዲ አረቢያ መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው እለት ወደሀገሪቱ ማዕከላዊ ግዛት የተተኮሰ ሚሳይል ማክሸፉን አስታውቋል። ሚኒስቴሩ አክለውም በምስራቅ ሪያድ ግዛት ሶስት ድሮኖችን ማክሸፉን ገልጿል።

የኳታር መከላከያ ሚኒስቴርም የአሜሪካ የጦር ሰፈር ያለበትን አል ኡዲያድ የአየር ኃይል ሰፈር ኢላማ ያደረጉ ድሮኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል።

እስራኤልና አሜሪካ በቴህራን የሚገኙ ኢላማዎችን እየደበደቡ ሲሆን ኢራንም የሚሳይልና የድሮን ጥቃቷን እንደቀጠለች ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠናን ያናጋው ይህ ጦርነት የመቆም አዝማሚያ ሳያሳይ አንድ ሳምንት ገደማ እያስቆጠረ ነው

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው