Loading...

የማላዊ መንግስት ጾታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን በማኮላሸት ለመቅጣት ሀሳብ አቀረበ

የማላዊ መንግስት ጾታዊ ጥቃታ በመፈጸም ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ  ግለሰቦችን በማኮላሸት(castration) ለመቅጣት ያቀረበው ሀሳብ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትችት ቀርቦበታል።

ጉዳዩ መነጋገሪያ የሆነው የሀገሪቱ ፓርላማ ጾታዊ ጥቃት የሚፈጽሙ ግለሰቦች በማኮላሸት ይቀጡ ወይስ አይቀጡ የሚል ውይይት ማድረጉን ተከትሎ መሆኑን ዶቼ ቬሌ ዘግቧል።

እንደዘገባው ከሆነ እንዳንድ የፓርላማ አባላት በአሁኑ ወቅት እየተፈጸመ ያለው የእስር ጊዜ ወንጀልን ለማስቀረት በቂ አይደለም የሚል መከራከሪያ አንስተዋል።

የማላዊ የጾታ፣ የህጻናት፣የአካል ጉዳተኞችና የማህበራዊ ዋስትና ሚኒስትር ማሪ ቶም ናቪቻ እንዲህ አይነት ቅጣት እንዴት እንደሚፈጸም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየመከረ ነው ብለዋል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ግን ምንም እንኳን በሀገሪቱ የአስገድዶ መድፈርና አካላዊ ጉዳት ማድረስ ተስፋፍቶ ቢቆይም ቅጣቶች ግን ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችና የሰብአዊ መብቶችን ያከበሩ መሆን አለባቸው ይላሉ።
ሀሳቡ ማላዊያን በሁለት ጎራ ከፍሎ እያከራከራቸው ይገኛል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው