ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኤክስ (X) ገጻቸው እንደገለጹት ከእስራኤል አቻቸው ጋር በሁለትዮሽና በቁልፍ ቀጣናዊ ክስተቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ውይይቱ መሪዎቹ በጋራ ጥቅማቸው ላይ ለመተባበር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያረጋገጡበት እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቅሰዋል።
ይህ ውይይት የተካሄደው በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ዳግም ግጭት በተቀሰቀሰበትና የኢትዮጵያና ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በገባበት ወቅት ነው።












