Loading...

ኬንያ ከሳፋሪኮም ድርሻዋ ውስጥ 15 በመቶውን ልትሸጥ መሆኑ ተገለጸ

ኬንያ ያጋጠማትን የፋይናንስ ክፍተት ለመሙላት 1.6 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለውንና 15 በመቶ የሚሆነውን የሳፋሪኮም ድርሻዋን ለደቡብ አፍሪካው  ቮዳኮም(ቪኦዲጄ-ጄ) ልትሸጥ መሆኑን የቴሌኮም ኩባንያው አስታውቋል።

ሀገሪቱ ያለባት ከፍተኛ እዳ፣ ታክስ ለመጨመር ያላት እድል ጠባብ መሆንና በየአመቱ የምትከፍለው እዳ የሀገሪቱን ገቢ 40 በመቶ መውሰዱ የኬንያ መንግስት ፊቱን የመንግስትን ንብረት እንዲሸጥ አስገድዶታል።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ የኬንያ ትልቁ ኩባያ የሆነው ሳፋሪኮም በናይኖቢ ካፒታል ገበያ (ሴኩሲቱ ኤክስቸንጂ) እለታዊ ግብይት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል። ቮዳኮም፣ በቮዳኮም ኬንያ በኩል የሳፋሪኮምን 39.9 በመቶ ድርሻ ይዛል።

ግዥው የቮዳኮምን ድርሻ ወደ 55 በመቶ ከፍ የሚያደርግ ሲሆን በዚህም የደቡብ አፍሪካው ኩባንያ በዋናነት ኤም-ፔሳ በተባለው የሞባይል የገንዘብ ዝውውር መተግበሪያ የሚታወቀውን ሳፋሪኮምን ወሳኝ በሆነ መልኩ እንዲቆጣጠር ያስችለዋል ተብሏል።ሽያጩ እውን ከሆነ የኬንያ መንግስት ድርሻም ከ35 በመቶ ወደ 20 በመቶ ዝቅ ይላል።  ሳፋሪኮም ኤችኤስቢሲ፣ኖርገስ ባንክና ሞቢየስን ጨምሮ በበርካታ ከለምአቀፍ ኩባንያዎች ባለቤትነት የሚተዳደር መሆኑን ዘገባው ኤልኤስኢጂን ዋቢ አድርጎ ጠቅሷል።

ሳፋሪኮም፣ ሳፋሪኮሞ ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ በሚል ቅርጫፍ ኩባንያ በኩል እ.ኤ.አ. ጁላይ 2021 ፍቃድ ካገኘ በኋላ በኦክቶበር 2022 ኢትዮጵያ ውስጥ በይፋ ስራ መጀመሩ ይታወሳል። በ10 አመታት ውስጥ 8.5 ቢሊየን ዶላር በኢትዮጵያ ፈሰስ እንደሚያደርግ የሚገልጸው ኩባንያ በአሁኑ ወቅተ (የ2ጂ፣ የ3ጂና የ4ጂ) የኢንተርኔትና ኤም-ፔሳ የተባለ የሞባይ የገንዘብ ዝውውር አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው