Loading...

የዶላር ዋጋ ዛሬ የ1.21% ቅናሽ አሳይቷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ግዙፍ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ የመሸጫ ዋጋ በ1.21 በመቶ ቅናሽ በማሳየት 153.25 ብር መውረዱን አስታውቋል። ይህ ክስተት በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ገበያ ታሪክ ውስጥ ብር ከዶላር አንጻር ዋጋው ሲያገግም የታየበት ብርቅዬ አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።

የጨረታው ውጤት በዝርዝር፦

  • የቀረበው መጠን፦ 500 ሚሊዮን ዶላር (በታሪክ ከፍተኛው መጠን)
  • የተጠየቀው መጠን፦ 455.29 ሚሊዮን ዶላር
  • ያልተሸጠ ዶላር፦ 44.71 ሚሊዮን ዶላር
  • አማካይ የምንዛሬ ዋጋ፦ 153.25 ብር (ባለፈው ሳምንት ከነበረው የ1.21% ቅናሽ አሳይቷል)
  • ዝቅተኛው (Cut-off) ዋጋ፦ 152.01 ብር

ገዢ ለምን ጠፋ? ባንኩ ለገበያው ካቀረበው 500 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 44.7 ሚሊዮን ዶላር ገዢ ሳይገኝለት መቅረቱ በኢኮኖሚ ባለሙያዎች ዘንድ “የገበያ መረጋጋት ምልክት” ተደርጎ ተወስዷል። የንግድ ባንኮች የቀረበውን ዶላር ሙሉ በሙሉ አለመግዛታቸው በገበያው ላይ የነበረው ከፍተኛ የዶላር ጥማት መረጋገጡን ወይም ደግሞ የንግድ ባንኮች ዶላር ለመግዛት የሚያስችል የብር ፈሳሽነት (Liquidity) እጥረት ሊገጥማቸው እንደሚችል አመላካች ነው።

እንደ ካፒታል እና ሌሎች የኢኮኖሚ ዘገባዎች ከሆነ የዶላር ዋጋ በ1.21 በመቶ መቀነሱ ባለፉት ሳምንታት በጥቁር ገበያና በባንኮች መካከል ይታይ የነበረውን ከፍተኛ የዋጋ ልዩነት ይበልጥ እንዲጠብ ያደርገዋል። ይህም አስመጪዎች በባንክ በኩል ዶላር ለማግኘት ያላቸውን ተስፋ ከፍ ያደረገ ሲሆን በሸቀጦች ዋጋ ላይ ሊታይ የሚችለውን የዋጋ ግሽበትም ሊገታ እንደሚችል ይጠበቃል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው