Loading...

ኢትዮጵያ ኤርትራ ጦሯን ከድንበር እንድታስወጣ አሳሰበች

የኤርትራ ጦር ድንበር አከባቢ የኢትዮጵያ ግዛት የሆኑ ቦታዎችን እንደያዘ በመግለጽ የኤርትራ መንግስት ጠሩን በአስቸኳይ እንዲያስወጣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

ጥር 30 2018 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጌዴዮን ጤሞቲዎስ ለኤርትራው አቻቸው በጻፉት ደብዳቤ “የኤርትራ መንግስት የአትዮጵያን ግዛት ከመያዝ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አማፂ ቡድኖችን ይደግፋል” በማለት ወንጅለዋል።

የደብዳቤው ሁለተኛ ክፍል በአንጻሩ የሰላም ጥሪን ያቀረበ ሲሆን ውይይት እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አገራቱ ካለፉበት “የግጭት እና አለመተማመን አዙሪት” የሚወጡበት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ይገልጻል።

ሚኒስቴሩ “ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማክበር ላቀረብነው ህጋዊ ጥያቄ ከኤርትራ አዎንታዊ ምላሽ ካገኘን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት፥ የባህር ጉዳዮችን እና የአሰብ ወደብ አጠቀማመን ጨምሮ ሁሉንም የጋራ ጉዳዮቻችንን ለመፍታት በቅን ልቦና ድርድር ለማድረግ ፈቃደኛ ነው” በማለት ለኤርትራ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው