Loading...

ኢራን የዩራኒየሟን ደረጃ ለመቀነስ ተስማማች

ኢራን ማዕቀቦች ከተነሱላት የበለፀገውን ዩራኒየም ለማለዘብ ዝግጁ እንደሆነች ገለጸች።

ኢራን አሜሪካ ሁሉንም ማዕቀቦች ካነሳች 60 በመቶ የበለፀገውን የኒውክሌር ዩራኒየም የጥንካሬ ደረጃ ለመቀነስ ወይም ለማቅጠን(dilute) ፈቃደኛ ትሆናለች ሲሉ የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ኃላፊ ሰኞ እለት ተናግረዋል

ኢራን ያስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ  አሜሪካ ከጣለችው ማዕቀብ በተጨማሪ በሌሎች የተጣሉትንም የሚያካት መሆኑ አልተገለጸም።

ኢራን በከፍተኛ ደረጃ የበለፀገውን ዩራኒየም መቀነስን(dilution) እንደመደራደሪያ ያቀረበችው ከአሜሪካ ጋር በኦማን ከተደረጉ ንግግሮች በኋላ ነው።

ዩራኒየምን dilute ማድረግ ማለት የበለጸገውን ንጥረ ነገር ደረጃውን ለመቀነስ ከሌላ ቁሳ ጋር መቀላቀል ማለት ሲሆን ይህም የመጨረሻው ምርት ከተወሰነ ማበልጸግ (enrichment) ገደብ እንዳይበልጥ ያደርገዋል።

ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ኒውክሌር ተቋሞች ላይ ጥቃት ከመሰንዘራቸው በፊት የኢራን ዩራኒየም ማበልጸግ ደረጃ ወደ 60 በመቶ ደርሶ የነበረ  ሲሆን ይህም እ.ኤ.አ. በ2015 ከአለም ኃያላን ሀገራት ጋር በተደረሰው የኒውክሌር ስምምነት ከተፈቀደው 3.67 በመቶ ገደብ እጅግ የላቀ ነው።  

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ድርጅት እንደገለጸው ኢራን  የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት ሳትሆን ዩራኒየምን 60 በመቶ የምታበለጽግ ብቸኛዋ ሀገር ነች።

ከጦርነቱ በፊት ኢራን እንዳላት የተገለጸው ከ400 ኪሎ ግራም በላይ የበለፀገ ዩራኒየም enrichment ደረጃው 90 በመቶ ከደረሰ ከዘጠኝ በላይ የኒውክሌር ቦምቦችን እንድትገነባ ያስችላታል።

 ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ኒውክሊየር ላይ የሚያስቀምጡት ቅድመ ሁኔታ ኢራን ሙሉ በሙሉ የማበልጸግ እገዳ እንዲጣልባት የሚጠይቅ ሲሆን ይህ በቴህራን ተቀባይነት የሌለው እና ከ 2015 ላይ ከተደረሰው ስምምነት በተለየ ለኢራን ምንም አይነት እድልን የማይሰጥ ነው።

ኢራን ሌሎች 190 ሀገራት ፈራሚዎች በሆኑበት የNuclear Non-Proliferation (የኒውክሊየር መስፋፋትን መግታት) ስምምነት ድንጋጌዎች መሰረት ኒውክሌርን ለሰላማዊ ጥቅም የማበልጸግ መብት እንዳላት ትናገራለች።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው