Loading...

ኬንያ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በማስተናገድ በአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሀገር ልትሆን ነው

Kenya to Make History as First African Host of World Athletics Championships in 2029

የኬንያዋ ዋና ከተማ ናይሮቢ የ2021 ዓ.ም. የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን እንድታስተናግድ ተመርጣለች። ይህም ኬንያን ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር የምታስተናግድ የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሀገር ያደርጋታል።
የአለም አትሌቲክስ የናይሮቢን መመረጥ ይፋ ያደረገው ማክሰኞ እለት በቡዳፔስት የምክር ቤት ስብሰባ ካደረገ በኋላ ነው።

የ2023 ዓ.ም. ሻምፒዮናን ደግሞ የጀርመኗ ሙኒክ ከተማ እንድታዘጋጅ ወስኗል።
የናይሮቢ መመረጥ የአፍሪካ አትሌቲክስ ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ተብሏል። ናይሮቢ የ2017 ዓ.ም. ሻምፒዮናን ለማስተናገድ ተጫርታ የነበረ ቢሆንም፣ የጃፓኗ ቶኪዮ በማሸነፏ ሳይሳካላት መቅረቱ ይታወሳል።

ውድድሩ በካሳራኒ ስታዲየም ይካሄዳል ስታዲየሙም በአሁኑ ወቅት እድሳት እየተደረገለት ነው። ናይሮቢ ቀደም ብሎ በ2009 ዓ.ም. የዓለም ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በ2013 ዓ.ም. የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመሳሰሉ ትልልቅ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ዝግጅቶችን አስተናግዳለች።
የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሴባስቲያን ኮ የናይሮቢን ጨረታ “አሳማኝ እና ስሜታዊ” በማለት ገልጸው፣ ሻምፒዮናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አፍሪካ መውሰድ ታሪካዊ ክስተት እንደሚሆን ተናግረዋል። በተጨማሪም ኬንያ ከአትሌቲክስ ጋር ያላትን ጥልቅ ትስስር በመጥቀስ፣ ስፖርቱ “በሀገሪቱ ማህበራዊ ሕይወት ውስጥ የተሰራ ነው” ብለዋል።

የ2021 ዓ.ም. ሻምፒዮና ኬንያ በድጋሚ ታላቅ ታሪካዊ ክስተት የምታስመዘግብበት ጊዜ ይሆናል። ኬንያ በዓለም የታወቁ ታላላቅ የርቀት ሯጮችን በማፍራት የምትታወቅ ሀገር ናት። ውድድሩን ማስተናገዷ ናይሮቢ የአፍሪካን አትሌቲክስ በዓለም ትልቁ መድረክ ላይ የምታሳይበትን እድል ይፈጥራል፤ እንዲሁም አፍሪካ ትልልቅ ዓለም አቀፍ የስፖርት ዝግጅቶችን ለማስተናገድ ያላትን አቅም የበለጠ ያጠናክራል

የ2023 ዓ.ም. ሻምፒዮና ወደ ጀርመን ይመለሳል። ውድድሩም በሙኒክ ኦሎምፒክ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህም ጀርመን ከ2001 ዓ.ም. በኋላ፣ በርሊን የሻምፒዮናውን ያስተናገደችበት ወቅት ጀምሮ፣ ውድድሩን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደገና ታስተናግዳለች ማለት ነው።

ሁለቱም የ2021 እና የ2023 ዓ.ም. ሻምፒዮናዎች በመስከረም ወር ይካሄዳሉ። ይህም ለ2019 ዓ.ም. በቤጂንግ ለሚካሄደው ሻምፒዮና የታቀደውን የውድድር መርሐ ግብር ተከትሎ ነው።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው