ታዋቂው የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአማር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል-እስላም መገደሉን አለምአቀፍ የመገናኛ ብዙኻን እየዘገቡ ነው።
የሰይፍ አል-እስላም ጠበቃ ካሊድ አልዛይዲና የፖለቲካ አማካሪው አብዱላ ኦትማን በትናንትናው እለት በትዊተር ገጻቸቸው ባጋሩት ጽሁፍ ዝርዝር ሳይሰጡ አል-እስላም መሞቱን አሳውቀዋል። አልጀዚራ ፋውሳል የተባለውን የሊቢያ ሚዲያ ጠቅሶ እንደዘገበው አል-እስላም ከሊቢያ ዋና ከተማ 136 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዚታን ውስጥ በመኖሪያ ቤቱ ነው የተገደለው።
የአል-እስላም የፖለቲካ ቡድን መሪ ቆየት ብሎ ባወጣው መግለጫ አራት ጭምብል ያጠለቁ ሰዎች ቤቱን ሰብረው በመግባት “በፍርሃትና በክህደት” ገድለውታል ብሏል። እንደመግለጫው ከሆነ ሰይፍ አል-እስላም አጥቂዎቹ ማንነታቸው እንዳይለይ የደህንነት ካሜራ ሲያጠፉ ግጭት ውስጥ ገብቷል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ያለው መቀመጫውን ትሪፖሊ ያደገው ከፍተኛ ምክርቤት የቀድሞ ኃላፊ ካሊድ አል-ምሽሪ ግድያው “በፍጥነትና በገለልተኝነት” እንዲመረመር ጠይቋል።
ሰይፍ አል-እስላም ሊቢያ ውስጥ ይፋዊ ስልጣን ባይኖረውም፣ በ2011 አባቱ ሙአማር ጋዳፊ ከአስርት አመታት የስልጣን ዘመን በኋላ በተቃዋሚዎች ሲገደሉ ዙፋን ወራሽ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ተቃዋሚዎች ትሪፖሊን በተቆጣጠሩበት ወቅት ወደ ሌሃ ሀገር ሊሸሽ ሲል ተይዞ ዚታን በተባለባቸው ከተማ ታስሮ ነበር። በ2017 በምህረት ከተቀቀ በኋላ ኑሮውን በእዚያው በዚታን አድርጎ ሲኖር ነበር ተብሏል።
በ1972 በትሪፖሊ የተወለደውና በምዕራቡ እንደተማረ የተነገረለት ሰይፍ አል-እስላም የአባቱ አስተዳደር ለውጥ የሚቀበል እንዲሆንና በ2000ዎቹ ሊቢያ ከምዕራባውያን ጋር ያላት ግንኙነት እንዲጠገን የራሱን ሚና ተወጥቷል።












