Loading...

ፈረንሳይ የመጀመሪያዋን የኢቦላ ተጠቂ መመዝገቧን አረጋገጠች

France detects first Ebola case in doctor returning from DRC - Afro Insight News

በኢቦላ የተጠቃው ይህ ግለሰብ በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰብዓዊ እርዳታ ሲሰጥ ቆይቶ የተመለሰ ዶክተር ነው ተብሏል።

ዶክተሩ ወዲያውኑ ወደ ልዩ ሆስፒታል መግባቱንና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሮይተርስ የፈረንሳይ ጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ ዘግቧል

ዲአርሲ የኢቦላ ወረርሽኙ የተከሰተው ባለፈው ወር እንደሆነ ብትገልጽም ባለሙያዎች ግን ቫይረሱ ከእዚያ በፊት ለሳምንት ያህል ሳይሰራጭ እንዳልቀረ ያምናሉ። በሀገሪቱ በቫይረሱ ከ260 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ1000 በላይ ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።

ባለፈው ወር በዲአርሲ በቫይረሱ የተያዘ አሜሪካዊ ዶክተር በጀርመን ሆስፒታል የታከመ ቢሆንም ይህ ህመም(case) በአውሮፓ ውስጥ ሲመዘገብ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ቫይረሱ ወደ ጎረቤት ዩጋንዳ ተስፋፍቶ ቢያንስ 20 ሰዎችን ማጥቃቱን የአለም ጤና ድርጅት ማረጋገጡ ይታወሳል

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው