Loading...

በቬኔዙዌላ በተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 900 ገደማ ደረሰ

Venezuela Earthquakes: Death Toll reaches 900 - June 2026 | Afro Insight News

አለምአቀፉ የነፍስ አድን ቡድን በቬንዙዌላ  በተከሰተውና በማግኒቲዩድ 7.2 እና 7.5 በተለካው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የተረፉ ሰዎች ለማውጣት ተቀላቅለዋል።

በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ያሉት ሀገራት ማለትም ሜክሲኮ፣ ብራዚል፣ካናዳ፣ ኩባና አሜሪካ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የነፍስ አድን ሰራተኞችን ሰብአዊ እርዳታ ማቅረባቸውን ዛሬም ቀጥለውበታል። የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት ከሆነ በአደጋው እስካሁን ህይወታቸው ያለፉት ሰዎች ቁጥር 920 ነው።

ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በሀገሪቱ በምዕተ አመት ውስጥ ከተከሰቱት ሁሉ ከፍተኛ መጠን ያለውና ንዝረቱ በአጠቃላይ ቀጠናው መድረሱን አለምአቀፍ የመገናኛ ብዙኻኖች ዘግበዋል። በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ ሌሎች 3000 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ካርሎስ አልቫራዶ እንደተናገሩት ሆስፒታሎች በቁስለኞች ተጨናንቀዋል።በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፍስራሾች ስር ተዘግተው እንደማይቀሩ ተሰግቷል።

በዋና ከተማ ካራካስ በስተሰሜን የምትገኘው ላ ጓይራ የተባለች ግዛት በከፍተኛ ሁኔታ ከተመቱት ግዛቶች አንዷ ነች። በእዚች ግዛት ከ100 በላይ ህንጻዎች ሲወድሙ፣ 70000 ቤተሰቦች ተጎጅ መሆናቸውን የቬንዙዌላ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ዶይስዳዶ ካቤሎ ተናግረዋል

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው