ኢራን የአውሮፓ አገራት ጦሮችን በአሸባሪነት ፈረጀች

ኢራን የአውሮፓ አገራትን ጦሮችን በአሸባሪነት የፈረጀች ሲሆን ውሳኔው የተላለፈው የአውሮፓ ህብረት የኢራን እስላማዊ ስርዓት ጠባቂ ህዋስ የሆነው IRGCን በአሸባሪነት መፈረጁን ተከትሎ ነው።

ኢራን የአውሮፓ ሀገራት ጦሮችን “አሸባሪ ቡድኖች” ብላ ፈርጃለች ሲሉ የፓርላማው አፈ-ጉባዔ እሁድ እለት ተናግረዋል።
አፈ-ጉባዔው መሀመድ ባገር ጋሊባፍ “IRGCን በአሸባሪ ድርጅትነት ለሚፈርጅ አካል አጸፋ ለመስጠት በወጣው ህግ አንቀጽ 7 መሰረት የአውሮፓ ሀገራት ጦሮች እንደ አሸባሪ ቡድን ይቆጠራሉ” ማለታቸውን የኢራን መንግስታዊ የዜና ጣብያ የሆነው IRNA ዘግቧል።

ይህ ዜና የተሰማው ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የኒውክሊየር ስምምነት እንድታደርግ ጫና እያደረጉ በሚገኙበት ሰዓታት ውስጥ ሲሆን፥ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አራን ለድርድሩ ፍቃደኛ እንደሆነች ገልጸዋል። ሆኖም ድርድሩን በጫና ስር ሆነው ማድረግ እንደማይችሉ አሳስበዋል።

ትራምፕ፥የጦር መርከቦችን ወደ ኢራን ወሰኖች እያስጠጉ እንደሆነ እና የኒውክሊየር ድርድሩን በተመለከተ የኢራን ባለስልጣናት ፍቃደኝነት ማሳየታቸውን ተናግረዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው