ከስልጣን የተነሱት የቬንዙዌላ መሪ ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤታቸው ሲሊያ ፍሎሬስ በአሜሪካ በድንገተኛ ጥቃት ከተያዙ በኋላ በኒውዮርክ የመጀመሪያቸው የፍርድ ቤት ውሏቸው በሰጡት ቃል “ጥፋተኛ” አይደለሁም ሲሉ ክደዋል።
ማዱሮ በዕጽ-ሽብርተኝነት ሴራ(Narco-terrorism conspiracy) ክስ ቀርቦበታል። ማዱሮ ከነባለቤቱ የቀረቡበት ክሶች የኮኬይን እጽ ዝውውር እና የጦር መሳሪያ ወንጀሎች ናቸው።
እራሱን በፍርድ ቤት “የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት” ብሎ እራሱን የገለጸው ማዱሮ ካራካስ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው “ተጠለፈን” እና “ተይዘን” ተወስደናል ብሏል።
በስፓኒሽ ቋንቋ አክሎም “እኔ የጦር እስረኛ ነኝ” ብሏል። የፕሬዝደንቱ ባለቤትም ፍሎሬስ እራሷን በፍርድ ቤት የቬንዙዌላ ቀዳማዊት እመቤት መሆኗን ተናግራለች።
የቬንዙዌላው ማዱሮ በአደንዛዥ ዕፅ ክስ ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ለአሜሪካ ፍርድ ቤት “አሁንም ፕሬዝዳንት ነኝ” ሲል ተናግሯል።
በተመሳሳይ፥ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቬንዙዌላ በአሜሪካ ቁጥጥር ስር ትሆናለች ያሉ ሲሆን ጊዜያዊ መሪዋ እንዲተባበሩ ካልሆነ ግን “በጣም ትልቅ ዋጋ” እንደሚከፍሉ አስጠንቅቀዋል።
በማዱሮ ስር የቬንዙዌላ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ዴልሲ ሮድሪጌዝ በዋና ከተማዋ ካራካስ የአገሪቱ አዲስ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
ትራምፕ አሜሪካ በቬንዙዌላ ያለውን ሰፊ የነዳጅ ክምችት ውስጥ ትይዛለች ብለዋል። ፕሬዝደንቱ በኮሎምቢያ፣ ሜክሲኮ እና ግሪንላንድ ላይ አዳዲስ ዛቻዎችን ያሰሙ ሲሆን በተለይም የኩባ አገዛዝ ውድቀት የማይቀር እንደሆነ ጠንካራ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።











