የማዱሮን እስር ተከትሎ የቬንዙዌላ ቀጣይ የመሪነት ስልጣንን ከፈልገች የኖቤል ሽልማቱን አሳልፋ ለእርሳቸው መስጠት ይኖርባት እንደሆን ጋዜጠኞች ለትራምፕ ጥያቄ አቅርብውላቸው ነበር።
ትራምፕ በርካታ ጦርነቶችን እንዳስቆሙ እና የተወሰኑትንም ከመከሰት እንዳስቀሩ በመጥቀስ ሽልማቱ የሚገባው ለእርሳው ብቻ እንደነበር ተናግረዋል።
ማሪያ ከትራምፕ ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ የያዘች ስትሆን የሽልማት ርክክቡ የግንኙነታቸው አንዱ አካል ሊሆን እንደሚችል ትራምፕ ግምታቸውን ገልጸዋል።
በተናጠል፥ ተቃዋሚዋ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የ2025 የኖቤል የሰላም ሽልማቷን ለአሜሪካው መሪ ልትሰጥ እንደምትችል ገለጻለች።
ማሪያ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረገችው ንግግር፥ ሽልማቱን አሳልፋ ለመስጠት ማሰቧ ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ተይዘው የነበሩትን የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን ከስልጣን በማንሳታቸው የቬንዙዌላ ህዝብ ለትራምፕ ያለውን ምስጋና ለመግለጽ በማሰብ እንደሆነ ገልጻለች።
ሽልማቱን ለማግኘት ፍላጎት እንዳላቸው ለረጅም ጊዜ ሲገልጹ እና ዲፕሎማሲያዊ ትርጉሙን አጉልተው ሲናገሩ የነበሩት ትራምፕ በሚቀጥለው ሳምንት በዋሽንግተን ሊደረግ በታቀደው ስብሰባ ማሪያ ሽልማቱን ብትሰጣቸው ደስተኛ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
ሆኖም የኖርዌይ ኖቤል ኢንስቲትዩት የኖቤል ሽልማት ሊተላለፍ፣ ሊጋራ ወይም ውድቅ ሊደረግ እንደማይችል ይገልጻል።
የኖቤል ፋውንዴሽን ይግባኝ የማይፈቅድ ህግን በመጥቀስ የኖቤል ሽልማትን ለመሸለም የተወሰነ ውሳኔ የመጨረሻ እና ቋሚ እንደሚሆን ፥ ኢንስቲትዩቱ በመግለጫው አስታውቋል። በተጨማሪም ተሸላሚዎች ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ በሚወስዱት እርምጃ እና መግለጫ ላይ ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት እንደሚቆጠብ ኢንስቲትዩቱ መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል።











