የናሳ አርቴሚስ 2 ጠፈተኞች መሬት ላይ አረፉ

በጨረቃ ላይ ለ 10 ቀናት አሰሳ ሲያደርጉ የቆዩት የአርቴሚስ 2 (Artemis ii) ጠፈርተኞች 40000 ኪሎ ሜትር በሰአት በኦሪዮን ስፔስ ካፕሱል(Orion Capasule) በመምዘግዘግ (Splash down) በፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ አርፈዋል።

ጠፈርተኞቹ ከወቅያኖሱ በሄሊኮፕተር በሳንዲያጎ ጠረፍ ወደሚገኘው ዩኤስኤስ ጆን ፒ. ሙሩታ ደርሰዋል።

የአርቴሚስ ተልክሶ በሰው ልጅ ታሪክ ከምድር ርቆ 252,856  ኪሎ ሜትር በመጓዝ ከዚህ  በአፖሎ 13 ተይዞ የነበረውን ክብረውስን በመስበር ታራክ ስርተዋል። በዚህ ተልእኮ ጠፈርተኞቹ ከጨረቃ በስተጀርባ በተጓዙበት ወቅት ከዚህ በፊት ያልታየውን ጎድጓዳ የጨረቃ ክፍል በማየታቸው ከዚህ በፊት ከነበሩት ተልእኮዎች ለየት ያደርገዋል።

በአዛዥ ሪድ ዊስማን የሚመራው ይህ ተልእኮ የመጀመሪያውን ጥቁር ቪክቶር ግሎቨር፣ የመጀመሪያዋን ሴት ክሪስቲና ኮክንና የመጀመሪያው አሜሪካዊ ያልሆነ ጠፈርተኛ ካናዳዊው ጄረሚ ሀንሰን ያካተተ ነበር።

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጉዞን “አስገራሚ” ነበር ብለውታል። ፕሬዝዳንቱ በጨረቃ ዙሪያ በመጓዝ “የዘመናዊ ጊዜ ፈርቀዳጅ” ሲሉ ጠፈርተኞቹን አወድሰዋል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው