የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ላይ በማህበራዊ ሚዲያ “ስም አጥፊ እና አዋራጅ” ጽሑፎችን አጋርተዋል ያላቸውን ከፍተኛ የእስራኤል ዲፕሎማት ከአገር እንዲወጡ አዝዟል።
የእስራኤል ኤምባሲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ በኤክስ (X) ገጻቸው ላይ ፕሬዝዳንት ራማፎሳን ከሽብርተኝነት ጋር የሚያገናኝ እና የግል ስብዕናቸውን የሚነካ ምስልና ጽሑፍ ካጋሩ በኋላ ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) በእስራኤል ላይ የመሰረተችውን የዘር ማጥፋት ክስ በመጥቀስ ፕሬዝዳንቱን “የሃማስ ተላላኪ” ሲሉ ፈርጀዋቸዋል።
የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስቴር (DIRCO) ዲፕሎማቱ የዲፕሎማሲያዊ ስነ-ምግባርን ጥሰዋል በሚል የ72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ሰጥቶ ከአገር እንዲወጡ አዟል።











