Loading...

ጦርነቱ ሰባት ቀናት ሲያስቆጥር፣ ኢራን ከፍተኛ የአየር ድብደባ ተፈጸመባት

እስራኤል ከአጋሯ አሜሪካ ጋር በመቀናጀት በኢራን ላይ የጀመረችው ጦርነት ሰባተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው እለት ቴህራንና ሌሎች የኢራን ከተሞች ከባድ የአር ድብደባ ደርሶባቸዋል።

ይህ ድብደባ የተፈጸመው የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፔቴ ሀግሴት በቴህራን ላይ የሚካሄደው የአየር ድብደባ እንደሚጨምር እያስጠነቀቁ ባለበት ወቅት ነው።

የእስራኤል ጦር በዛሬው እለት በቴህራን ላይ በጀመረው አዲስ የአየር ድብደባ ዘመቻ “የአገዛዙን መሰረተልማት” ኢላማ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን አሜሪካ ደግሞ ቢ-2 የተባለውን ዘመናዊ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን በመጠቀም በጥልቀት የተቀበሩ የባለስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፊያዎችን ኢላማ አድርጌያለሁ ብላለች።

አልጀዚራ እንደዘገበው በዋና ከተማዋ ቴህራን በመኖሪያ መንደሮች አካባቢና በቴህራን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጨምሮ በበርካታ ቦታዎች ከፍተኛ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል። ከዚህ በተጨማሪም የኢራን ወታደራዊ ትምህርት ቤትም ጥቃት ደርሶበታል ተብሏል።

እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ እየፈጸሙት ባለው ጥቃት የኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሚኒ፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና ከ1000 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል። ኢራን በእስራኤልና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ባሉባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ እያደረሰች ባለው የአጸፋ እርምጃ የሰው ህይወትን ያጠፉና በረራን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮችን ያስተጓጎሉ የሚሳይልና የድሮን ጥቃቶች እያደረሰች ትገኛለች።

ሩሲያና ቻይናን ጨምሮ የተወሰኑ ሀገራት እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ እያደረሱ ያለውን ጥቃት በግልጽ ያወገዙ ሲሆን አብዛኛው የአለም ክፍል ግን ጦርነቱ ቀጠናዊ መልክ መያዙ እንዳሰጋው ከመግለጽ ውጭ አቋም አልያዘም

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው