ትራምፕ የጃፓኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ያስደነገጧቸው ምን ብለው ነው?

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳኔ ታካያቺ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ አሜሪካ አቅንተው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነት እያካሄዱ ባለበት ወቅት ወደ አሜሪካ ያቀኑት የቶኪዮና የዋሽንግተንን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በማሰብ ነው።

ነገርግን የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕና ታካያቺ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ትራምፕ ለአንድ ጃፓናዊ ጋዜጠኛ የሰጡት ምላሽ ሌላ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።

ጋዜጠኛው ትራምፕን “በኢራን ላይ ጦርነት እንደምትከፍቱ እንደ ጃፓን ለመሳሰሉት የአውሮፓና የእስያ አጋሮቻችሁ ለምን ቀድማችሁ አላሳወቃችሁም? እኛ ጃፓኖች ግራ ተጋብተናል” ሲል ጠይቋል።  ትራምፕም “እኛ ሳናሳውቅ ነገሮችን መጨረሰ(Surprise) ማድረግ እንፈልጋለን”፣ ደግሞስ ከጃፓን በላይ ስርፕራይዝ ማድረግ የሚፈልግ ማን አለ” አሉ።

ትራምፕ ቀጠል አድርገው “እናንተ(ጃፓኖች) የፒርል ሀርቦር ጥቃትን ለምን ቀድማችሁ አላሳወቃችሁንም” ብለው ፈገግ ሲሉ በተቃራኒው ታካያቺ በድንጋጤ ሽምቅቅ ሲሉ ተስተውለዋል።

ትራምፕ የጠቀሱት በሁለተኛ የአለም ጦርነት ወቅት(1941) የጃፓን ኢምፔሪያል ናቪ አየር ሰርቪስ በአሜሪካ ሀዋይ በፒርል ሀርቦር ላይ ያደረሰውን ድንገተኛ ጥቃት ነው። ይህ የጃፓን ድርጊት አሜሪካ በይፋ ወደ ሁለተኛው የአለም ጦርነት እንድትገባ ያደረገ ክስተት ነበር።

ይህን ጥቃት ለመበቀል ጊዜ ስትጠብቅ የነበረችው አሜሪካ በ1945 በሁለቱ የጃፓን ከተሞች ሄርሽማና ናጋሳኪ ላይ የኑክሌር ቦምብ በመጣል ታሪካዊ ወድመት አድርሳለች። ይህ ጃፓን እጅ እንድትሰጥና ሁለተኛው የአለም ጦርነትም እንዲጠናቀቅ ምክንያት መሆኑ ይታወቃሳል።

አሜሪካና ጃፓን አሁን ላይ የታሪክ ቁርሿቸውን ወደ ጎን በመተው ጠንካራ ፖለቲካዊ ወዳጅነት መስርተዋል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው