Loading...

ትራምፕ ሰላማዊ ሽግግር እስከሚደረግ ድረስ አሜሪካ ቬንዙዌላን “ትመራለች” አሉ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር እስከሚደረግ ድረስ አሜሪካ ቬንዙዌላን እንደምታስተዳድር ተናግረዋል።

ፕሬዝደንቱ ይህን ያሉት የአሜሪካ ጦር በቬኔዙዌላ ዋና ከተማ ከራካስና በወታደራዊ ይዞታዎች ላይ መጠነሰፊ ጥቃት ፈጽሞ ፕሬዝደንት ማዱሮንና ባለቤታቸውን በቁጥጥር ስር አውሎ በአሜሪካ ክስ ከመሰረተ በኋላ በሰጡት መግለጫ ነው።

ቀደም ብሎ የቬንዙዌላ መንግስት ድብደባውን ተከትሎ በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አውጆ ነበር።

አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ መጠነሰፊ ጥቃት የፈጸመችው ፕሬዝደንት ትራምፕ ማዱሮ ወደ አሜሪካ አደገኛ አደንዛዥ እጽ የሚያሰገባ ወንበዴ ቡድን ይመራሉ የሚል ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ካሰሙ ከወራት በኋላ ነው።

ባለፉት ሳምንት የአሜሪካ ጦር ዋነኛ የገቢ ምንጭ የሆኑትን የነዳጅ መርከቦች መያዟን ተከትሎ ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ነበር።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው