የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) በገንዘብ ቀውስ ምክንያት ህውልውናው አደጋ ላይ እንደወደቀ ዋና ጸሃፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናግረዋል።
“ቀውሱ በመባባስ ላይ ነው” ሲሉ ጉተሬዝ ለአባል አገራት ያሳወቁ ሲሆን ፈጣን እርምጃ ካልተወሰደ የተቋሙ ገንዘብ በሃምሌ ወር እንደሚያልቅ ተገልጿል።
ተቋሙ በድረ ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ መሰረት፥ ለገንዘብ ቀውሱ እንደ ምክንያት ያቀረበው ሁለት ምክንያቶች ያልተከፈሉ መዋጮዎች እና እስካሁን ድረስ ተቋሙ ጥቅም ላይ ያላዋለውን ገንዘብ መልሶ ለአባል አገራት በብድር መልክ እንዲሰጥ የሚያስገድደውን ህግ ነው።
የተመድ ከፍተኛ ለጋሽ የሆነችው አሜሪካ ግማሽ ያህል የሚሆነውን የግዴታ መዋጮዋን እንዳልከፈለች ተገልጿል።
“ሁሉም አባል አገራት የሚጠበቅባቸውን የአባልነት መዋጮ በተገቢው መልኩ ይከፍላሉ ወይም የፋይናንስ ህጉ እንዳዲስ መጻፍ ይኖርበታል።” በማለት ዋና ፀሐፊው ለአባል ሀገራት ሁለት አማራጮች አቅርበዋል።












