እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ እያካሄዱት ባለው ዘመቻ ሶሰት የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውንና ሌሎች አምስት መቁሰላቸውን የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ (ሴንትኮም) በዛሬው እለት አስታውቋል።
አሜሪካ በኢራን ላይ እያካሄደችው ካለው “ታላቁ የውጊያ ዘመቻ” ጎን ለጎን በቴህራን በሚደገፉት የሀውቲ ታጣቂዎች ላይ የምታደርገውን ጥቃት እንደቀጠለች ነው።
ሴንትኮም እንደገለጸው ተጨማሪ የአሜሪካ ጦር አባላት ወደ ምድብ ቦታቸው በሚመለሱበት ወቅት በፍንጥርጣሪዎች ተመተው መጠነኛ ጉዳት አጋጥሟቸዋል።
የአሜሪካ ጦር በቀጣናው እየተካሄደ ያለው ዘመቻ መቀጠሉንና ሁኔታዎች ተለዋዋጭ መሆናቸውን ገልጿል።
እስራኤል ከአጋሯ አሜሪካ ጋር በመሆን በኢራን ላይ መጠነሰፊ የአየር ጥቃት በመክፈት የኢራኑን ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሚኒን ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናትንና 200 ገደማ ንጹሃንን መግደሏ ተዘግቧል። ኢራን ወደ እስራኤልና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ወደአሉባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚሳይል ናዳ በማዝነብ የሰው ህይወትን የቀጠፈና በረራዎችን እያስተጓጎለ የአጸፋ ጥቃት ፈጽማለች።












