ዚምባብዌ የውጭ ዜጎች በተወሰኑ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ እንዳይሳተፉ የሚያግድ ህግ አወጣች

በደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል የምትገኘው ዚምባብዌ የውጭ ዜጎች ለሀገር ውስጥ ዜጎች በተተው 17 የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ እንዳይሰማሩ የሚያግድ ህግ ማውጣቷን አስታውቃለች።

ዘ ዚምባቡዌውያን የተባለው የኦንላይን ጋዜጣ እንደዘገበው በዚህ ህግ መሰረት የውጭ ዜጎች በጌጣጌጥ ማምረት፣ በዳቦ ቤት፣በማስታወቂያ ስራ፣ በውበት ስራ እና በእደ ጥበብ እና እጀ ስራ መስኮች እንዳይሰሩ ይከለክላል።

ከተዚህ በተጨማሪም ይህ ህግ በውጭ ባለሀብቶች የተያዙ በተወሰኑ ዘርፎች ያሉ ኩባንያዎች አብዛኛውን ድርሻቸውን በሶስት አመት ውስጥ ለሀገሪቱ ዜጎች እንዲያስረክቡ እንደሚያስገድድ ዶቼቨለ ዘግቧል።

እንደዘባው ከሆነ በዚህ ህግ የተካተቱ ኩባንያዎች ከታህሳስ 2025 ጀምሮ እስከ 2028 ድረስ 75 በመቶ የሚሆነውን ድርሻቸውም ለሀገሪቱ ዜጎች ማስረከብ ወይም መዝጋት ይጠበቅባቸዋል። የውጭ ባለሀብቶች እንዳይሳተፉ ክልከላ የተጣለባቸው በትንንሽ ዘርፎች ላይ ሲሆን በትልልቅ ዘርፎች ላይ ግን አሁን መስራት ይችላሉ።
ነገርግን ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎች መስራት የሚችሉት ብዙ ገንዘብ ፈሰስ ካደረጉና ቢያንስ ከ100 በላይ የሀገሪቱን ዜጎች ከቀጠሩ ነው።
የሀገሪቱ መንግስት እንደገለጸው የባንክና የግዙፍ ማዕድን ቁፋሮ ስራዎች አሁንም ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ናቸው።
ታንዛኒያም በተመሳሳይ የውጭ ባለሀብቶችን ያገለለ ውሳኔ ባለፈው ሰኔ ወር አሳልፋ ነበሮ።

ታንዛኒያ ባወጣችው “የቢዝነስ ላይሰንስ ኦርደር” አሰራር መሰረት የውጭ ዜጎች የችርቻሮ ንግድ፣ የአስጎብኚ ስራ፣ የጽዳት፣የአነስተኛ የማዕድን ማውጣትን ስራን ጨምሮ በ15 ትንንሽ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ እንዳይሳተፉ ከልክላለች። ሀገሪቱ ይህ ያደረገችው የዜጎቿ የስራ እድል አማራጭ እንዲሰፋ ነው የሚል ምክንያት በወቅቱ አቅርባለች።

ዚምባቡዌና ታንዛኒያው የውጭ ባለሀብቶችን ሊያርቁ ይችላሉ የተባሉ ህጎችን ሲያወጡ፣ ሌሎች ሀገራት በአንጻሩ የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ በማለም አዲስ ህግ ያወጣሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ሰኔ ወር የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ በማለም፣ የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል ህግ ባውጣቱ ይታወሳል። መንግስት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውንና በርካታ ተቃውሞ የቀረበበት ይህን ህግ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ማጸደቅ ችሏል።አንድ የውጭ ዜጋ ኢትዮጵያ ውስጥ የቤት ባለቤት መሆን የሚችለው ቢያንስ ከ150 ሺ ዶላር በላይ ኢንቨስት ሲያደርግ መሆኑን ህጉ ይጠቅሳል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው