Loading...

በማዳጋስካር ወታደራዊ ወረራውን ተከትሎ ሐገሪቱ ከአፍሪካ ሕብረት ታገደች።

  • አፍሮ ኢንሳይት ዜና

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በወታደራዊ ወረራ የጊዜው ፕሬዝዳንት የሆኑትን አንድሪ ራጆኤሊናን ከስልጣን ካባረረ በኋላ የአፍሪካ ህብረት ማዳጋስካርን አግዷል።

የCAPSAT ክፍል ኃላፊ ኮሎኔል ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ወረራውን የመሩት ሲሆን አርብ ዕለት በጊዜያዊ መሪነት ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት ርምጃው ኢ-ህገ መንግስታዊ ነው ሲል አውግዞ በፍጥነት ወደ ሲቪል አገዛዝ እንዲመለስ ጠይቋል።

የሕብረቱ ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ እንዳሉት “ ሕብረቱ ከሕገመንግስት ውጪ በኃይል የተወለዱ መንግስታትን እውቅና አይሰጥም ሲል” በመፈንቅለ መንግስት ላይ ያለውን የዜሮ መቻቻል አቋም በድጋሚ አረጋግጧል።

ለተጨማሪ ዜናዎች የአፍሮ ኢንሳይት ገፆችን ይከታተሉ።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው