የምርጫ ኮሚሽኑ ፕሬዝደንት ሳሚያ ምርጫውን በ98 ፐርሰንት አሸንፈዋል ብሏል። ምርጫው ፍትሃዊ አይደለም የሚሉ ወጣት ሰልፈኞች ፣ መንግስት ዋነኛ ተቃዋሚዎችን ከምርጫው በማገድ ዴሞክራሲዊ ሥርዓትን አፍኗል ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
የታንዛኒያ መንግስት በተቃውሞው የተገደሉት 2 ሰዎች ብቻ ናቸው ሲል ታማኝ የመረጃ ምንጮች የሟቾች ቁጥር 500 እንደሆነ ተናግረዋል።
የአገሪቱ የመከላከያ ሃይሎች ዋና አዛዥ ጃኮብ ምኩንዳ “…የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ወንጀለኞች ናቸው፥ ሰልፉም የወንጀል ድርጊት በመሆኑ መቆም አለበት” ብለዋል።












