Loading...

በቬንዙዌላ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ 1400 በላይ አለፈ

Venezuela, Caracas, LaGuaira Earthquake death toll reaches 1400

በቬንዙዌላ በተከሰቱት ሁለት ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር እስከ ቅዳሜ ድረስ ከ 1400 በላይ ማለፉንና በአደጋው በከፍተኛ መጠን በተጠቁት የጠረፍ አካባቢዎች የሚደረገው የነፍስ አድን ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ይህ ቁጥር ይፋ የሆነው የነፍስ አድን ሰራተኞች፣ የተጠቂ ቤተሰቦችና በጎ ፈቃደኞች የላጓይራና የተወሰኑ የካራካስ ቦታዎችን በህይወት የተረፉ ሰዎችንና አስከሬኖችን ለማግኘት አሰሳ እያደረጉ ባለበት ወቅት ነው።

የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት ከ1600 በላይ የውጭ በጎ ፈቃደኛ የነፍስ አድን ሰራተኞች የደረሱ ሲሆን ተጨማሪ ሌሎች በመንገድ ላይ ናቸው። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የአሜሪካ ሄሊኮፕተሮች የነፍስ አድን ሰራተኞችን በአደጋው በከፍተኛ መጠን ወደተጎዱት የላጓይራ ቦታዎች አሳርፏል።

ሮይተርስ ያናገራቸው ነዋሪዎች በተወሰኑ አካባቢዎች ያለው የነፍስ አድን ስራ በቂ አለመሆኑን ገልጸዋል። አደጋው ከፍተኛ ድንጋጤ እንደፈጠረባቸው የተናገሩት ነዋሪዎች፣ አደጋው ከተፈጠረበት ምሽት ጀምሮ መንገድ ላይ እያደሩ እንደሆነም ተናግረዋል።

የጠፉት 55 ሺ ሰዎች

ምንምእንኳን መንግስት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ቢገልጽም በሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚተዳደረው ዌብሳይት ግን የጠፉት ሰዎች ከ55ሺ በላይ እንደሆኑ ዘርዝሯል።

በላቲን አሜሪካ በተከሰተውና በማግኒቲዩድ 7.5 እና 7.2 በተለካው በዚህ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስከ 10 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ህይወታቸው ሊያልፍ እንደሚችል የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ግምቱን አስቀምጧል። አደጋው ራሳቸውን የለውጥ አቀንቃኝ አድርገው ለሚመለከቱትና የኒኮላስ ማዱሮን በአሜሪካ መንግስት መወገድ ተከትሎ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ለሆኑት ዴልሲ ሮድሪጊዝ ፖለቲካዊ እንደምታ ይኖረዋል ተብሏል

አሜሪካ አደጋውን ተከትሎ ለቬንዙዌላ ድጋፍ እየላከች ነው። አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን በትናንትናው እለት የትራምፕ አስተዳደር ከላከው 150 ሚሊየን ዶላር በተጨማሪ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የድጋፍ ማእቀፍ በቀናት ውስጥ ይፋ ይሆናል ብለዋል

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው